‹‹መኑ ያኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ፤ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማን ነው?›› (ሮሜ.፰፥፴፭)
By:
ማኅበረ ቅዱሳን
On
09/07/2023Reading time:
12 min
Summary:
‹‹መኑ ያኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ፤ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማን ነው?›› (ሮሜ.፰፥፴፭)
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በፍጹም እምነት አምላኩን የሚወድ ቢኖር መራብም፣ መጠማትም፣ መታረዝም፣ መደብደብም፣ መታሰርም ሆነ መገደል ቢሆን ይህንን ፍቅረ እግዚአብሔር የሚለይ ምንም ነገር ሊኖር እንደማይችል በዚህ አንቀጽ አስረድቷል፡፡ ሐምሌ ፭ የሚዘከረውም በዓል ቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ሃይማኖታቸው ምክንያት በሮማው ንጉሥ ኔሮን ሰማዕትነት የተቀበሉበትን በማሰብ ነው፡፡ በየዓመቱ የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍትም በዚህ ዕለት ይከበራል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ
ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡንና ታንኳውን እንዲሁም አባቱን እርግፍ አድርጐ ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው።
ቅዱስ ጴጥሮስ የሐዋርያት አለቃ ሆኖ ተሹሟል፡፡ ለአገልግሎት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በእስያ፣ በሮም፣ በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ በገላትያና በሌሎችም አገሮች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በስብከቱ ምክንያትም ልዩ ልዩ መከራን ተቀብሏል፡፡ በክርስቶስ ኀይል በመታመኑ በክርስቶስ ስም ጣቢታን ከሞት አስነሥቷል፤ ይህም አንዱ ድንቅ ተአምራቱ ነው (ሐዋ.፱፡፴፮)፡፡ ከተሰጠው ጸጋ ብዛት የተነሣ በጥላው ሕሙማን ይፈወሱ ነበር (ሐዋ. ፭፥፲፭)፡፡ ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ትምህርት በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ሁለት መልእክታትን ጽፏል፡፡ (፩ኛእና ፪ኛ ጴጥሮስ)
የቅዱስ ጴጥሮስ በሰማዕትነት
በቅዱስ ጴጥሮስ ምድራዊ የአገልግሎት ዘመን የክርስቲያኖች ጠላት የነበረው የሮም ንጉሥ ወደ አካይያ ዘምቶ ድል አድርጎ በደስታ ወደ ሮሜ ሲመለስ መኳንንቱን ለማስደሰት፣ ጣዖታቱንም ለማክበር ሲል በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዓወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሀገሪቱ መኳንንት እንዳይገድሉት ትጥቁን ለውጦ ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ሣለ በተገለጸለት ጊዜ ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?›› በማለት ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹ዳግም ልሰቀል ወደ ሮም እሔዳለሁ›› አለው፡፡ ‹‹ዳግመኛ ትሰቀላለህን?›› ባለው ጊዜም ‹‹አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው›› በማለት መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሔድ ነበር፡፡ ስትሸመግል እጅህን ታነሣለህ፤ ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደ ማትወደውም ይወስድሃል›› በማለት አሟሟቱን የሚያመለክት መሆኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ፡፡ (ዮሐ.፳፩፥፲፰)
ቅዱስ ጴጥሮስ ዜግነቱ ሮማዊ ስላልነበረ በግርፋትም፣ በእስራትም በሞትም እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡ እንደ ሥርዓታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን ‹‹እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይሆን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ሐምሌ ፭ ቀን ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ በመስቀል ላይ ሳለም ተከታዮቹን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ካዘዛቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ሥጋውንም መርቄሎስ የሚባለው ደቀ መዝሙሩ ሽቱ ቀብቶ፣ በነጭ ሐር ገንዞ ዛሬ ቫቲካን በምትባለዋ ስፍራ በክብር ቀብሮታል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ
ቅዱስ ጳውሎስ የጥንቱ ስሙ ‹ሳውል› ይባል ነበር፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ደግሞ በ ፲፭ ዓመት ዕድሜው በገማልያ ትምህርት ቤት በመግባት የአይሁድን ሕግና ሥርዓት ተምሯል፡፡ በ፴ ዓመቱም የአይሁድ ሸንጎ አባል ሆኗል፡፡ (፩ኛቆሮ.፩.፲፯፣ሐዋ.፳፪.፫) ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ሕገ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን ተምሯል፡፡ ለኦሪታዊ እምነቱ ቀናተኛ በመሆኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር፡፡ በ፴፪ ዓመት ዕድሜውም ከኢየሩሳሌም ሁለት መቶ ሃያ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ ከባለሥልጣናቱ አገኘ፡፡ ለሕገ ኦሪት ቀናኢ ከመሆኑ የተነሣም የክርስቶስ ተከታዮችን ሁሉ ያሳድድ ነበር፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተደብድቦ በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ የገዳዮቹ ልብስ ጠባቂ ነበር፡፡ (ሐዋ.፯፥፶፰፣ ፳፪፥፳) ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ሲሔድ ከመንገድ ላይ ለሐዋርያነት ተጠርቷል፡፡ (ሐዋ.፱፥፩-፴፩፣፳፪፥፩-፳፩) ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በመላው ዓለም እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳምኗል፡፡ ሲሰብክም ጣዖት አምላኪ፣ ሕመምተኛ፣ ችግረኛ፣ አረማዊና አይሁዳዊ እየመሰለ ብዙዎችን አስተምሮ ለእግዚአብሔር መንግሥት አዘጋጅቷል:: (፩ኛቆሮ.፱፥፲፱-፳፫) ዐረብ፣ አንጾኪያ፣ እልዋሪቆን፣ ሊቃኦንያ፣ ሦርያ፣ ግሪክና ልስጥራን ካስተማረባቸው አገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ወንጌልን በመስበኩ ምክንያትም ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራና ሥቃይ ደርሶበታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ጸጋ ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ በልብሱ ቅዳጅም ሕሙማን ይፈወሱ ነበር፡፡ (ሐዋ.፲፱፥፲፩) ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ሌላ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ፲፬ መልእክታት አሉት፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነት አገልግሎቱን ሊፈጽም ሲልም የሮም ንጉሥ ኔሮን ቄሣር የክርስቲያኖች ቍጥር እየጨመረ የመጣው በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመማረካቸው ምክንያት መሆኑን ተረድቶ፣ ይልቁንም የቤተ መንግሥቱ ሰ

Fየቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነት አገልግሎቱን ሊፈጽም ሲልም የሮም ንጉሥ ኔሮን ቄሣር የክርስቲያኖች ቍጥር እየጨመረ የመጣው በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመማረካቸው ምክንያት መሆኑን ተረድቶ፣ ይልቁንም የቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሳይቀር በቅዱስ ጳውሎስ በመማረካቸው ተቈጥቶ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ፍርድ ሸንጎው አስቀረበው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋር መስቀሉን ይዞ ንጉሡንና ወታደሮችን ሳይፈራ የኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነትና አምላካዊ ሥልጣን ይመሰክር ነበር፡፡ ንጉሡም በቍጣ እንዲሞት ፈረደበት፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ሮማውያን የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የሚቀጣው ሰው የሌላ አገር ዜጋ ከሆነ ከፍርዱ ውጪ ተጨማሪ ቅጣት ይቀጡትና ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን የሮም ዜግነት ስለ ነበረው ሳይገርፉ በአንድ ቅጣት ብቻ በሰይፍ እንዲገደል ወስነውበታል፡፡ ወደሚገደልበት ስፍራ ሲወስዱትም በንግግሩና በአስተያየቱ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይበትም ነበር፡፡ እንዳውም በጦርነት ድል አድርጎና ማርኮ እንደ ተመለሰ ወታደር ይደሰት ነበር እንጂ፤ ለሚገድሉትም ይቅርታን ይለምን ነበር፡፡
በገዳዮቹና በተከታዮቹ ፊትም የክርስትና ሽልማቱ የእግዚአብሔር መንግሥት መሆኑን የሚያስገነዝብ ቃል እያስተማረ እግዚአብሔር የሚሰጠውን የጽድቅ አክሊል ለመቀበል ይቻኮል ነበር፡፡ (፪ኛቆሮ. ፬፥፮-፲፰) ወታደሮች ሊገድሉት ሲወስዱትም ከንጉሥ ኔሮን ወገን የሆነችውን የአንዲት ብላቴና መጐናጸፊያ ‹‹ዛሬ እመልስልሻለሁ›› ብሎ ከተቀበላት በኋላ ‹‹መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፡፡ ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ፤ ወደፊትም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል›› በማለት ራሱ በመልእክቱ እንደ ተናገረው ፊቱን በብላቴናዋ መጐናጸፊያ ተሸፍኖ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ አገልግሎቱን በሰማዕትነት ፈጽሟል፡፡ (፪ኛጢሞ.፬፥፯-፰)
ደቀ መዛሙርቱም ራሱን ከአንገቱ ጋር ቢያደርጉት እንደ ቀድሞው ደኅና ሆኖላቸው በክብር ገንዘው ቀብረውታል፡፡ ሰያፊው ቅዱስ ጳውሎስን እንደ ገደለው ለመናገር ወደ ንጉሡ ሲመለስም ያቺ መጐናጸፊያዋን የሰጠችው ብላቴና ‹‹ጳውሎስ ወዴት አለ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ራሱን ተቈርጦ በመጐናጸፊያሽ ተሸፍኖ ወድቋል›› ሲላት ‹‹ዋሽተሃል፤ እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ በኩል አልፈው ሔዱ፤ እነርሱም የመንግሥት ልብስ ለብሰዋል፤ በራሳቸውም በዕንቍ ያጌጡ አክሊላትን አድርገዋል፤ መጐናጸፊያዬንም ሰጡኝ፤ ይህችውም እነኋት፤ ተመልከታት›› ብላ ሰጠቸው፤ ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው፤ አይተውም አደነቁ፤ ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፡፡ ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ጨለማውን ዓለም በማድመቃቸው ‹ብርሃናተ ዓለም› ተብለው ይጠራሉ፤ የቅዱሳኑ አገልግሎት፣ ገድላቸው እና ተአምራቸው በመጽሐፈ ስንክሳር፣ በዜና ሐዋርያት እና በገድለ ሐዋርያት
Here are some ways yoga could benefit your health, plus how to get started (stretched lycra optional):
Yoga body benefit #1
It will increase your memory. If crossword puzzles and Sudoku have been the extent of your memory training to now, it could be time to sharpen up your warrior pose. The UCLA research took brain scans and memory tests comparing the effects of 12 weeks of memory exercises and a course of yoga and meditation on 25 adults over 55. The latter not only improved their spatial and visual memories but also reduced depression and anxiety and increased resilience to stress.
Subscribe to our newsletter
Subscribe our newsletter to get weekly updates.