
About us
እንኳን ደህና መጡ
ትምህርቱ በብቃት እና በጥራት እየሰጠን እንገኛለን፡፡ ወላጆች እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እያደርጋችሁት ያለውን ድጋፍ በእጅጉ እንድትጨምሩ እንማጸናለን! ህልወተ እግዚአብሔርን ስራዓተ ቤ/ክርስቲያንን እንድሁም ተዕዛዛቱን ከወዲሁ በጨቅላ እድሚያቸው ካልቀረጽን በኋላ እንደማይቻል ያለፈብን ትውልድ ግልጽ ምስክራችን ነው እናም ኑ እና ልጆቻችንን እግዚአብሄር የለሽ እና ልቅ ሆኖ ከሚኖር የትውልድ ችግር ውስጥ ተረባርበን እንውጣቸው፡፡
በ2023 የበጋ ትምህርት ላይ የተባበሩን ወጣቶች በጥቂቱ
እንድምን አላችሁ የበጋ ተማሪዎች እኛ አሁን እናንተ በምትማሩበት ወንበር ላይ ተቀምጠን እንደ እናንተ ፊደል ቆጥረን ተንተባትበን አንብበን በየጊዜው የሚሰጠውን ትምህርት እና ስራዓተ እምልኮን ሳናቋርጥ ነው ዛሬ ለደረሰንበት አገልግሎት የበቃነው ለዚህም እኛን ሲይስተምሩ የነበሩ አሁንም በማስተማር ላይ የሚገኙ የህጻናት ክፍል አስተማሪዎቻችን እና ወላጆቻችን ምስጋና ይድረሳቸው፡፡ እኛም የተደረግልንን ድካም በማሰብ በተራችን ታናናሾቻችንን ከ 2022 የበጋ ትምህርት ጀምሮ በማስተማር እየረዳን እንገኛለን ለዚህም ያበቃን አምላካችንን እናመሰግናለን ፡፡






